• News

 • News

 • ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም አውስትራሊያ በሚኖሩ ስድተኞች ተሸለሙ! Posted on 22 October 2014

  ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም አውስትራሊያ በሚኖሩ ስድተኞች በተመሰረተው ‘ዲሞክራሲ ፎር ኢትዮጵያ ሰፖርት ግሩፕ’ የተሰኘ ቡድን ያዘጋጀውን ሽልማት ለመቀበል ሰሞኑን ወደ አውስትራሊያ መሄዳቸውን ተገለጸ፡፡
  ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም በአገሪቱ ሁሉን አቀፍ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ለማስቻል ለረጅም አመታት ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ያለው ቡድኑ፣ ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና ለመስጠት በማሰብ ሽልማቱን  እንዳበረከተላቸው አስታውቋል፡፡ 
  ፕሮፌሰሩ ሽልማቱን ከመቀበላቸው በተጨማሪ፣ሰሞኑን በሚልቦርን፣ በሲድኒ፣ በብሪስባኔና በሌሎች የአውስትራሊያ ከተሞች ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር በአገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡
  በሰብዓዊ መብቶች፣ በታሪክ፣ በጂኦግራፊና በልማት ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ የተለያዩ መጽሃፍትንና የጥናት ወረቀቶችን የጻፉትና ለረጅም አመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነትና በተለያዩ የመንግስት ድርጅቶች ያገለገሉ ፕ/ር መስፍን፣ ከኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ መስራቾች አንዱ ሲሆኑ፣ ለተለያዩ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አማካሪ ሆነው ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

  « Back to news archive